Fana: At a Speed of Life!

ባንኩ የራሳቸው ያለሆነን ገንዘብ ወስደው ወደ ቤቲንግ ተቋማት ያዘዋወሩ ግለሰቦች እንዲያመለክቱ አሳሰበ

 

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ያለ አግባብ የራሳቸው ያለሆነን ገንዘብ ከባንኩ ወስደው ወደ ቤቲንግ ተቋማት ያዘዋወሩ ሰዎች ባንክ በመገኘት ለዚሁ የተዘጋጀውን ቅጽ በመሙላት እንዲያመለክቱ አሳሰበ፡፡

ባንኩ መጋቢት 6 ቀን 2016 ባጋጠመው የሲስተም ችግር ምክንያት ያለአግባብ የገንዘብ ልውውጥ እንደነበር አስታውሷል።

በዚህም በርካታ ግለሰቦች በጥሬ ገንዘብ እና በዲጂታል የክፍያ አማራጮች የወሰዱትን ገንዘብ እየመለሱ እንደሚገኙም ገልጿል፡፡

ሆኖም አንዳንድ ግለሰቦች የወሰዱትን ገንዘብ ወደ ቤቲንግ ተቋማት በማዛወራቸው መመለስ እንደተቸገሩ መጠቆማቸውንም ጨምሮ አስታውቋል፡፡

በዚህም “ገንዘቡን ተመላሽ ማድረግ እንዲቻል ወደ ቤቲንግ ተቋማት የራሳችሁ ያልሆነውን ገንዘብ ያዘዋወራችሁ አቅራቢያችሁ በሚገኝ የባንካችን ቅርንጫፍ በመገኘት ለዚሁ የተዘጋጀውን ቅጽ በመሙላት እንድታመለክቱ እናሳስባለን” ሲል መልዕክቱን አስተላልፏል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.