Fana: At a Speed of Life!

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ግብርና ቢሮ መሬት ወስደው ሥራ ባልጀመሩ አልሚዎች ላይ እርምጃ እወስዳለሁ አለ

አዲስ አበባ፣መጋቢት 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በምርጥ ዘር ብዜት ላይ ለመሰማራት መሬት ወስደው ሥራ ባልጀመሩ አልሚዎች ላይ እርምጃ እንደሚወስድ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ግብርና ቢሮ አስታወቀ፡፡

የምርጥ ዘር ብዜት ሥራ ለማከናወን ስድስት ባለሃብቶች መሬት መውሰዳቸውን እና ሦስቱ ወደ ሥራ አለመግባታቸውን የቢሮው ምክትል ኃላፊ አጥናፉ ባቡር ገልጸዋል፡፡

ወደ ምርት ያልገቡበትን ምክንያት የመለየት ሥራ እየሠሩ መሆናቸውንም ነው ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት የተናገሩት፡፡

በዚህ ሂደትም ሁለት አማራጮች መኖራቸውን ጠቁመው፤ የመጀመሪያው የያዙትን መሬት እንዲያለሙ ማድረግ ሲሆን ሁለተኛው አማራጭ ግን መሬቱን ለሌሎች አልሚዎች መስጠት እንደሆነ አብራርተዋል፡፡

መሬት ከወሰዱት አልሚዎች መካከል ሦስቱ ወደ ሥራ መግባታቸውን እና በዚህም 720 ሔክታር መሬት በዘር መሸፈኑንም አስታውሰዋል፡፡

እስካሁንም 20 ሺህ ኩንታል ምርጥ ዘር ተሰብስቦ ወደ ምርት ማበጠሪያ ማዕከላት መግባቱን ነው ያመላከቱት፡፡

በሰሎሞን ይታየው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.