Fana: At a Speed of Life!

በጌዴኦ ዞን ገደብ ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ3 ሰዎች ሕይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጌዴኦ ዞን ገደብ ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የሶስት ሰዎች ሕይወት አለፈ፡፡

አደጋው ከረፋዱ 5 ሰዓት ላይ ከዲላ ከተማ ወደ ገደብ ሲጓዝ የነበረ ተሽከርካሪ በተቃራኒው ከገደብ ወደ ዲላ ከሚሄድ የሕዝብ ማመላለሻ አውቶቡስ ጋር በመጋጨቱ ነው የተከሰተው፡፡

በአደጋውም የሶስት ሰዎች ሕይወት ያለፈ ሲሆን÷ በሌሎች ተሳፋሪዎች ላይም ከባድ እና ቀላል ጉዳት መድረሱን የወረዳው ፖሊስ መረጃ ያመላክታል፡፡

ቀላልና ከባድ ጉዳት የደረሰባቸው ተጎጂዎች በገደብ ሆስፒታል ሕክምና እየተደረገላቸው መሆኑም ተጠቁሟል፡፡

በተያያዘ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ዳውሮ ዞን ሎማ ቦሳ ወረዳ በተከሰተ የትራፊክ አደጋ የሁለት ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በአንድ ሰው ላይ ከባድ ጉዳት ደርሷል፡፡

አደጋው የደረሰው ከኮንታ ዞን ኮይሻ ወረዳ 140 ኩንታል እህል ጭኖ ወደ ወላይታ ሶዶ ሲጓዝ የነበረ የደረቅ ጭነት ተሽከርካሪ ኤላ ባቾ ቀበሌ ሲደርስ በመገልበጡ ነው።

ጉዳት የደረሰበት ግለሰብ በታርጫ ሆስፒታል የሕክምና ክትትል እየተደረገለት መሆኑን ከሎማ ቦሳ ወረዳ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.