Fana: At a Speed of Life!

አሜሪካ በንግድ፣ ኢኮኖሚ ልማትና ኢንቨስትመንት ከኢትዮጵያ ጋር ለመስራት እንደምትፈልግ አስታወቀች

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አሜሪካ በንግድና ኢኮኖሚ ልማት እንዲሁም ኢንቨስትመንት ዙሪያ ከኢትዮጵያ ጋር በጋራ ለመስራት እንደምትፈልግ ገለጸች፡፡

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ገብረመስቀል ጫላ በአሜሪካ ኤምባሲ የንግድ አማካሪ ሌኦን ሻርሺንስኪ ጋር ሁለቱ ሀገራት በንግዱ ዘርፍ በትብብር በሚሰሩባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል፡፡

በቆይታቸውም ፥ አሜሪካ በንግዱ ዘርፍ ባሉ መልካም ተሞክሮዎች፣ በንግድ ፖሊሲ፣ በአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ ንግድ ቀጣና እና የዓለም ንግድ ድርጅትን የሚያካትት ስልጠና መስጠት በምትችልበት ሁኔታ ላይ ከስምምነት ደርሰዋል፡፡

የኢትዮጵያ ንግድና ፋይናንስ ዘርፍ ለውጪው የግል ዘርፍ ክፍት እየሆነ መምጣቱን ተከትሎ የአሜሪካን ባለሃብቶች መጥተው እንዲሳተፉ ጥሪ አቅርበዋል ሚኒስትሩ፡፡

አክለውም ፥ የሀገሪቱን የግል ዘርፍ አቅም ለማጎልበት የሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ አሜሪካ ድጋፍ እንድታደርግ ለአማካሪው መግለጻቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

የንግድ አማካሪው ሌኦን ሻርሺንስኪ በበኩላቸው ፥ አሜሪካን በንግድና ኢኮኖሚ ልማት እንዲሁም ኢንቨስትመንት ከኢትዮጵያ ጋር በጋራ ለመስራት ያላትን ፍላጎት አሳይተዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.