Fana: At a Speed of Life!

በትራፊክ አደጋ የ3 ሰዎች ሕይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 28፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ገብረ ጉራቻ ከተማ ሀርቡ በሪ ቀበሌ ድልድላ አካበቢ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የሦስት ሰዎች ሕይወት አለፈ፡፡

ዛሬ ጠዋት 3 ሠዓት ላይ በደረሰው የትራፊክ አደጋ ከሟቾች በተጨማሪ በሁለት ሰዎች ላይ ከባድ ጉዳት መድረሱን የገብረ ጉራቻ ከተማ ፖሊስ ጽ/ቤት የትራፊክ ደኅንነት ተቆጣጣሪ ምክትል ሳጅን ደረጄ ሶሮምሳ ተናግረዋል፡፡

ጉዳት የደረሰባቸው ወገኖችም በኩዩ አጠቃላይ ሆስፒታል የሕክምና ዕርዳት እያገኙ ነው ማለታቸውን የሰሜን ሸዋ ዞን ፖሊስ መምሪያ መረጃ አመላክቷል፡፡

 

የአደጋው መንስዔም ከተፈቀደው ፍጥነት በላይ ማሽከርከር መሆኑን ነው ያመላከቱት፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.