Fana: At a Speed of Life!

በክልሉ የአርብቶ አደሩን ህይወት ለመቀየር የሚያስችሉ ተግባራት ትኩረት ተሰጥቷቸዋል ተባለ

 

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የአርብቶ አደሩን ህይወትና አኗኗር ለማሻሻል የተጀመረው ተግባር በትኩረት እየተከናወነ መሆኑ ተገለፀ፡፡

የክልሉ አርብቶ አደርና ቆላማ አካባቢ ልማት ቢሮ በቆላማ አካባቢ ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት (LLRP) በምዕራብ ኦሞ ዞን በተለያዩ አካባቢዎች በመከናወን ላይ የሚገኙ የልማት ስራዎች ተጎብኝተዋል።

በጉብኝቱ ላይ የተገኙት የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና ግብርና ቢሮ ሀላፊ አቶ ማስረሻ በላቸው÷ በፕሮጀክቱ የአርብቶ አደሩን ህይወት ለመቀየር የተከናወኑ ተግባራት አበረታች በመሆናቸው ማጠናከር ያስፈልጋል ብለዋል።

የክልሉ አርብቶ አደርና ቆላማ አካባቢዎች ልማት ቢሮ ሀላፊ አቶ ታምሩ ቦኒ÷ ፕሮጀክቱ ትምህርት ቤትና የመስኖ አውታርን ጨምሮ በርካታ ተግባራትን እያከናወነ ነው ብለዋል።

የቆላማ አካባቢ ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት አስተባባሪ የሆኑት አቶ ደረጄ በቀለ÷ ፕሮጀክቱ የአርብቶ አደሩን ኑሮ ለማሻሻል የጀመራቸው ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልፀዋል።

በጉብኝቱ ላይ የክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ ቤት ሀላፊ አቶ ፀጋዬ ማሞን ጨምሮ ሌሎች የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።

አብዱ ሙሃመድ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.