Fana: At a Speed of Life!

ብሪክስ አማራጭ ዓለም አቀፍ የገንዘብ ስርዓት መፍጠር አለበት – አምባሳደር ቻም ኡጋላ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ብሪክስ አማራጭ ዓለም አቀፍ የገንዘብ ስርዓት መፍጠር እንዳለበት በሩሲያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ቻም ኡጋላ ኡሪያት ገለጹ፡፡

አምባሳደር ቻም ኡጋላ ከሩሲያው መገናኛ ብዙሃን አርቲ ጋር በነበራቸው ቆይታ እንዳሉት፥ የብሪክስ አባል ሀገራት ኢኮኖሚያቸውን ለማጠናከር በጋራ መስራት አለባቸው፡፡

ለዚህም ዓለም አቀፍ የገንዘብ ስርዓት መፍጠር አንድ አማራጭ መሆኑን አመላክተዋል።

መቀመጫውን በሻንጋይ ያደረገው ኒው ልማት ባንክ በብሪክስ የተቋቋመውና በፈረንጆቹ 2015 ለንግድ ስራ የተከፈተው “ለብሪክስ አባል ሀገራት አስተዋፅዖ ያበረክታል” ሲሉ አንስተዋል አምባሳደሩ፡፡

ከኢትዮጵያ፣ ከብራዚል፣ ከቻይና፣ ከግብፅ፣ ከሕንድ፣ ከኢራን፣ ከሩሲያ፣ ከደቡብ አፍሪካ፣ ከተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች የተውጣጡ የፓርላማ አባላትና አምባሳደሮች የሩሲያ ኤክስፖ ላይ ተገኝተው ጉብኝት አድርገዋል፡፡

ጉብኝቱ ባለፉት ቀናት በተካሄደው የብሪክስ ሀገራት የዓለም አቀፍ ጉዳዮች ኮሚቴ ሰብሳቢዎች ጉባኤ አካል እንደሆነም ነው የተገለጸው፡፡

ቀደም ሲል ሩሲያ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ቻይና ፣ ሕንድና ብራዚልን ያቀፈው ብሪክስ በቅርቡ ኢትዮጵያን ጨምሮ ኢራን፣ ግብፅ እና የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች መቀላቀሉ ይታወሳል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.