Fana: At a Speed of Life!

የጅምላና ችርቻሮ ንግድን ለውጭ ባለሃብቶች ክፍት ለማድረግ የተያዘው እቅድ ሸማቹን ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ተመለከተ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የጅምላ እና ችርቻሮ ንግድን ለውጭ ባለሃብቶች ክፍት ለማድረግ የተያዘው እቅድ በተለይ ሸማቹን ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ምሁራን ገለጹ፡፡

በሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ የፋይናንስ እና ፖለቲካል ኢኮኖሚ ተመራማሪ ደጀኔ ለማ (ዶ/ር)እንዳሉት÷ንግዱን ለውጭ ባለሃብቶች ክፍት ማድረጉ ከንግድ ትርፍ እና የንግድ ሰንሰለት ጋር በተያያዘ ህብረተቡ ላይ እየተፈጠሩ ያሉ ጫናዎችን ለማስወገድ እድል ይፈጥራል።

በሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ መምህር እና ተመራማሪ መኮንን ከሳሁን(ዶ/ር) በበኩላቸው ÷ገበያው ለውጭ ባለሃብት ክፍት ሲደረግ ሸማቹ የተሻለ የዋጋ ቅናሽ እና ጥራት ያለውን እቃ በብዙ አማራጭ እንዲያገኝ ያስችለዋል ብለዋል፡፡

አዲሱ አሰራር ከፍተኛ የትርፍ ምጣኔ የለመዱ የሀገር ውስጥ ባለሃብቶችን በውድድር ወደ መሰመር ሊያስገባ እንደሚችልም ነው ምሁራኑ የገለጹት፡፡

የውጭ በለሃብቶቹ ሀገር ውስጥ ገብተው እንዲነግዱ ከመፍቀደ ባሻገር ወደ ምርት የሚገቡበትን አሰራሮች በመፍጠር መደገፉ የተሻለ ወጤት ሊያስገኝ ይችላልም ነው ያሉት።

በትዕግስት አብርሀም

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.