Fana: At a Speed of Life!

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ተመሰረተ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የምስረታ ጠቅላላ ጉባዔ ተካሂዷል፡፡
የክልሉ ርዕሰ መሥተዳድር ጥላሁን ከበደ በጉባዔው ላይ ባደረጉት ንግግር÷ ቀይ መስቀል ሰው ተኮር ሥራዎችን በሰብዓዊነት እና በቅንነት ድጋፍ የሚያደርግ ተቋም መሆኑን አስረድተዋል፡፡
የዜጎችን ሁለንተናዊ ብልጽግና ለማረጋገጥ በሚከናወኑ ሥራዎች የቀይ መስቀል ማኅበር ሚና የጎላ መሆኑን አንስተው÷ በሰው ሰራሽ እና በተፈጥሮ አደጋ ለተጎዱ ወገኖች የሰብዓዊ ድጋፍ እየሰጠ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር ፕሬዚዳንት አበራ ቶላ በበኩላቸው÷ማኅበሩ የመንግሥት ደጋፊ መሆኑን አስታውቀው እርስበርስ መደጋገፍ እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡
በኢብራሂም ባዲ እና መለሠ ታደለ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.