Fana: At a Speed of Life!

የሸዋል ዒድ በዓልን ምክንያት በማድረግ የተዘጋጀ የባህል ዐውደ ርዕይና ፌስቲቫል ተከፈተ

 

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሸዋል ዒድ በዓልን ምክንያት በማድረግ የተዘጋጀ የባህል ዐውደ ርዕይና ፌስቲቫል በሐረር ከተማ ዛሬ ተከፈተ።

የባህል ዐውደ ርዕዩና ፌስቲቫሉ የተከፈተው የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ፣ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር አቶ ቀጄላ መርዳሳ፣ የቱሪዝም ሚኒስትር አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ እና ሌሎች እንግዶች በተገኙበት ነው።

በባህል ዐውደ ርዕዩና ፌስቲቫሉ አጎራባች ክልሎች እና የአርጎባ የባህል ቡድን እንዲሁም የባህል አልባሳትና ጌጣጌጥ አምራች ማህበራትና ተቋማት ተሳትፈዋል።

የሸዋል ዒድ በዓልን አስመልክቶ የተዘጋጀው የባህል ዐውደ ርዕይና ፌስቲቫል የብሔር ብሔረሰቦችን ግንኙነት እንደሚያጠናክር የሐረሪ ክልል የባህል፣ ቱሪዝምና ቅርስ ቢሮ ሃላፊ አቶ ተወለዳ አብዶሽ ተናግረዋል።

“ሸዋል ዒድ ለህብረ ብሔራዊ አንድነታችንና ለቱሪዝም እድገታችን” በሚል መሪ ሐሳብ የተዘጋጀው የባህል ዐውደ ርዕይና ፌስቲቫል ለሁለት ቀናት እንደሚቆይም ጠቁመዋል።

በተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ የሳይንስና ባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) በማይዳሰስ የዓለም ቅርስነት መመዝገቡን የሚገልጽና ከዩኔስኮ የተሰጠ የሸዋል ዒድ የምስክር ወረቀት ቢል ቦርድ በክብር እንግዶቹ መመረቁን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.