Fana: At a Speed of Life!

በትራፊክ አደጋ የ5 ሰዎች ህይወት አለፈ

 

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ካፋ ዞን ጨና ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የአምስት ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በ13 ሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱ ተገለፀ፡፡

አደጋው ዛሬ ከጠዋቱ 3 ሰዓት ከ30 ከዋቻ ወደ ቦንጋ እየተጓዘ ያለ ዶልፊን ተሸከርካሪ እና ከሚዛን ወደ አዲስ አበባ ሲጓዝ የነበረ ሲኖ ትራክ ተሸከርካሪ በጨና ወረዳ ቦባ በላ ቀበሌ በመጋጨታቸው የደረሰ ነው፡፡

በደረሰው የትራፊክ አደጋ የአምስት ተሳፋሪዎች ህይወት ሲያልፍ በ13 ሰዎች ላይ ጉዳት ደርሷል፡፡

የአደጋው መንስኤ የሚጣራ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን÷ ቦታው በተደጋጋሚ ጊዜ አደጋ የሚደርስበት ስፍራ በመሆኑ አሽከርካሪዎች ጥንቃቄ እንዲያደርጉ መልዕክት ተላልፏል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.