Fana: At a Speed of Life!

አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ከደቡባዊ ትብብር ድርጅት ዋና ጸሃፊ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ከደቡባዊ ትብብር ድርጅት ዋና ጸሃፊ ሼክ መንሱር ቢን ሙስሰላም ጋር ተወያይተዋል።

በውይይታቸውም በኢትዮጵያ እና በድርጅቱ መካከል ትብብርን የበለጠ ማሳደግ በሚቻልበት ሁኔታ እንዲሁም ከደቡባዊ ትብብር ድርጅት ጋር ተቀራርቦ መስራት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መክረዋል፡፡

መቀመጫውን አዲስ አበባ የያደረገው ድርጅቱ እውቀትን በማፍለቅ እና አካታች የትምህርት ስርዓት እንዲገነባ በዓለም አቀፍ ደረጃ እየሰራ እንደሚገኝ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

ድርጅቱ በደቡብ ደቡብ ማዕቀፍ በአባል ሀገሮቹ መካከል የትምህርት፣ የቴክኒክ እና የገንዘብ ትብብር ለመፍጠር እያገለገለ ነውም ተብሏል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.