Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያና ጂቡቲ የኢሚግሬሽን መረጃ ልውውጥ ትብብራቸውን ለማጠናከር ተስማሙ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያና ጂቡቲ በኢሚግሬሽን መረጃ ልውውጥ እና ድንበር ቁጥጥር ላይ ያላቸውን ትብብር በይበልጥ ለማጠናከር ተስማሙ፡፡

የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ሰላማዊት ዳዊት ከጂቡቲ የሀገር ውስጥ ሚኒስትር ሰዒድ ኑህ ሀሰን ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም ከኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት በተጨማሪ ከድንበር ቁጥጥር ጋር በተያያዘ ያሉ ትብብሮችን ወደ ተሻለ ደረጃ ለማሸጋገር በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡

ምክክር ከተደረገባቸው ጉዳዮች ጋር የተያያዙ ክፍተቶችን በመለየት ብሎም የነበሩ ትብብሮችን በይበልጥ ለማጠናከር ከስምምነት መድረሳቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.