Fana: At a Speed of Life!

አሜሪካ ለብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን ሥራዎች ድጋፍ እንደምታደርግ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን እያከናወናቸው ያሉትን ተግባራት ለመደገፍ የአሜሪካ መንግሥት ዝግጁ መሆኑን በኢትዮጵያ የሀገሪቱ አምባሳደር ኤርቪን ጆሴ ማሲንጋ አረጋገጡ፡፡

የብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን ኮሚሽነር ተመስገን ጥላሁን ከአምባሳደር ኤርቪን ጆሴ ማሲንጋ ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም ኮሚሽኑ የተሰጠውን ተልዕኮ ለማሳካት እያከናወናቸው ያሉ ተግባራትን ኮሚሽነር ተመስገን አብራርተዋል።

ለኮሚሽኑ ሥራ ስኬት አጋር አካላት እያደረጉት ያለው ትብብር የሚደነቅ መሆኑን በመግለጽ በቂ አለመሆኑንና ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አንስተዋል፡፡

የአሜሪካ መንግሥትም ለተቋሙ ሥራ ውጤታማነት ድጋፉን አጠናክሮ እንዲቀጥል መጠየቃቸውን የኮሚሽኑ መረጃ አመላክቷል፡፡

አምባሳደር ማሲንጋ በበኩላቸው ለኮሚሽኑ ተልዕኮ ስኬት የአሜሪካ መንግሥት ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.