Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከ762 ሚሊየን ብር በላይ ማስመለሱን አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ያለአግባብ ከተወሰደበት ገንዘብ ውስጥ ከ762 ሚሊየን ብር በላይ ማስመለሱን አስታውቋል፡፡

ከሲስተም ጋር በተገናኘ መጋቢት 6 ቀን 2016 ዓ.ም በተፈጠረ ችግር ምክንያት ብር 801 ሚሊየን 417 ሺህ 747ብር ከ81 ሳንቲም ያለአግባብ ተወስዶ እንደ ነበር ተገልጿል፡፡

ከዚህም ገንዘብ ላይ 762 ሚሊየን 941ሺህ 341 ብር ማስመለስ ተችሏልም ብሏል፡፡

ይህም መሰብሰብ ከነበረበት ገንዘብ ውስጥ 95 በመቶ የሚሸፍን ነውም ብሏል ባንኩ፡፡

ቀሪውን 5 በመቶ ወይም 38 ሚሊየን 474 ሺህ 938 ብር ተመላሽ ካላደረጉ ግለሰቦች የማስመለስ ሥራው እንደሚቀጥልም ነው ባንኩ በማህበራዊ ትስስር ገጹ ያስታወቀው፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.