Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ በዓለም አቀፉ የታዳሽ ኃይል ኤጄንሲ ጉባዔ ላይ እየተሳተፈች ነው

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) 14ኛው ዓለም አቀፉ የታዳሽ ኃይል ኤጄንሲ ጉባዔ በተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች አቡ ዳቢ በዛሬው ዕለት ተጀምሯል፡፡

በጉባዔው የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስትር ሃብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር ኢ/ር) እና በተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች የኢትዮጵያ አምባሳደር ዑመር ሁሴን (ዶ/ር) ኢትዮጵያን በመወከል ተሳትፈዋል፡፡

በጉባኤው ከታዳሽ ኃይል እና የአየር ንብረት ለውጥ ጋር በተያያዘ በርካታ ሪፖርቶች ቀርበው ውይይት እንደሚደረግባቸው በተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመላክታል፡፡

ለሁለት ቀናት በሚካሄደው ጉባኤ የሒደት ሪፖርት፣ የፓናል ውይይት እንዲሁም የአባል ሀገራት መግለጫ እንደሚቀርብም ተጠቁሟል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.