Fana: At a Speed of Life!

የሐረሪ ክልል የዳያስፖራ ቤት ልማት ዘርፍ ውጤቱን በሌሎችም ለመድገም እንደሚሰራ ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሐረሪ ክልል በዳያስፖራ ቤት ልማት ዘርፍ ያስመዘገበውን ውጤት በሌሎች የኢንቨስትመንት ዘርፎችም ለመድገም እንደሚሰራ ተገልጿል፡፡

በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን አቅምና ፍላጎትን ማስተናገድ የሚያስችሉ የዳያስፖራ ተሳትፎ ጥቅሎችን ከባለድርሻዎች ጋር በቅንጅት ለመለየትና ለመቅረጽ በክልሎችና ከተማ አስተዳደድሮች ውይይት እየተካሄደ ነው፡፡

በሐረሪክ ክልል በመካሄድ ላይ ባለው ውይይት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት ሃላፊ ጃሚዕ መሐመድ፥ የዳያስፖራውን ሁለንተናዊ ተሳተፎ ለማሳደግ እንቅስቃሴ እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል።

ክልሉ በዳያስፖራ ቤት ልማት ዘርፍ በሰራው ስራ ውጤታማ መሆኑን አስታውሰው፤ ይህንን ውጤት በሌሎች የኢንቨስትመንት ዘርፎች ለመድገም የዳያስፖራ ተሳትፎ ጥቅሎችን በማዘጋጀት የሚሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

የዳያስፖራውን ተሳትፎ ከማሳደግ ጋር በተያያዘ ቀጥተኛ ግንኙነት ያላቸው ባለድርሻ አካላት በተገኙበት እየተካሄደ ባለው መድረክ በኢትዮጵያ ዳያስፖራ አገልግሎት የተዘጋጀው የዳያስፖራ ተሳትፎ ጥቅል ቀረጻ ጠቋሚ ሰነድ ቀርቦ ውይይት የተደረገበት ነው።

ተሳታፊዎችም በአስተያየታቸው ጠቋሚ ሰነዱ አሁን ያለውን ነባራዊ ሁኔታና የሀገሪቱን የልማት ጥያቄ መሰረት አድርጎ የተዘጋጀ መሆኑን ማንሳታቸውን ከዳያስፖራ አገልግሎት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በዚህም ዳያስፖራው ራሱንና ትውልድ ሀገሩን መጥቀም እንዲችል በሰነዱ መነሻነት የክልሉን የኢንቨሰትመንት አቅም በአግባቡ የለየና ዳያስፖራውን በልዩ ሁኔታ ሊያሳትፍ የሚችል የልማት ጥቅል ተቀርፆ ወደ ስራ መግባት እንደሚያስፈልግም ነው የተገለጸው።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.