Fana: At a Speed of Life!

የግብርና ምርት ማቀነባበሪያ ኢንዱስትሪዎችን መደገፍ እንደሚገባ ተጠቆመ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የግብርና ምርት ማቀነባበሪያ ኢንዱስትሪዎችን መደገፍ እንደሚያስፈልግ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል ገለጹ፡፡

አቶ መላኩ አለበል ከተባበሩት መንግስታት የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት የዘላቂ ልማት ግብቦች ፈጠራ እና ኢኮኖሚ ትራንስፎርሜሽን ዳይሬክተር ጉንተር በገር ከተመራ ልዑክ ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም÷በግብርና ምርቶች ማቀነባበሪያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ላይ በማተኮር ኢኮኖሚውን ለማሳደግ ሀገር አቀፍ አጋርነት ፕሮግራም አተገባበር፣ ዘላቂ የልማት አቅምን ማሳደግ ዓላማው ያደረገ የልህቀት ማዕከል ለማቋቋምና ሌሎች የጋራ ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል፡፡

አቶ መላኩ÷ከተመድ የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት ጋር የተተቀናጀ የግብርና ምርቶች ማቀነባበሪያ ኢንዱስትሪ ፖርኮችን ውጤታማ በማድረግ የአርሶና አደሩን ኑሮ ለማሻሻል በሚደረገው ጥረት ተስፋ ሰጭ የትብብር ስራዎች እየተሰሩ ነው ብለዋል።

አግሮ ኢንዱስትሪ ፓርኮች አነስተኛ አርሶ አደሮች ጥራት ያለው የግብርና ምርት በማምረትና ለኢንዱስትሪዎች በማቅረብ የኢኮኖሚ አቅማቸውን ለማሳደግ አስተዋፅኦው የላቀ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

የግብርና ትራንስፎርሜሽንን ለማሳለጥ የግብርና ምርት ማቀነባበሪያ ኢንዱስትሪዎችን መደገፍ ያስፈልጋል ማለታቸውንም የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

ጉንተር በገር በበኩላቸው÷ለሀገር አቀፍ አጋርነት ፕሮግራም አተገባበር፣ ዘላቂ የልማት አቅምን ማሳደግ ዓላማው ያደረገ የልህቀት ማዕከል ለማቋቋም የተደረሰው ስምምነት ፍሬ እንዲያፈራ ለማድረግ ከባለድርሻ አካላት ጋር እንደሚሰሩ ገልፀዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.