የደቡብ ዕዝ መረጃ መምሪያ በክትትል የያዘውን ከ30 ኩንታል በላይ አደንዛዥ ዕፅ አስወገደ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ዕዝ መረጃ መምሪያ በምዕራብ አርሲ ዞን ሻላ ወረዳ ባደረገው ክትትል የያዘውን ከ30 ኩንታል በላይ ካናቢስ የተሰኘ አደንዛዥ ዕፅ ማስወገዱን አስታወቀ።
የዕዙ ወታደራዊ ወንጀል ምርመራ እና የወንጀል ክትትል ቡድን መሪ ተወካይ ሻለቃ ብርሃኑ ተረፈ እንዳስታወቁት፤ ከ30 ኩንታል በላይ ካናቢስ እና 2 ኩንታል የካናቢስ ዘር ተይዞ በእሳት በማቃጠል እንዲወገድ ተደርጓል፡፡
አደንዛዥ ዕጹ ለአሸባሪው ሸኔ የጥፋት ተልዕኮ የገቢ ምንጭ ሆኖ ሊያገለግል እንደነበር ማስረዳታቸውን ከመከላከያ ሠራዊት የማኅበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡