የብሪክስ ትብብርን ለማጠናከር ያለመ መድረክ እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ እና ሩሲያ የጥናትና ምርምር ተቋማት የባለሙያዎች ቡድን የብሪክስ ትብብርን ማጠናከር የሚያስችል የምክክር መድረክ በአዲስ አበባ እያካሄደ ነው፡፡
በመድረኩም የብሪክስ ትብብርን ማጠናከር የሚያስችሉ በአካባቢ ጥበቃና የአየር ንብረት ለውጥ፣ በግብርና፣ ሳይንስና ቴክኖሎጂ፣ በፋርማሲቲካል ኢንዱስትሪ እና ሌሎች ጉዳዮች ላይ ጽሑፎች ቀርበው ምክክር እየተደረገ ነው፡፡
የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር በየነ ጴጥሮስ (ፕ/ር)፣ የውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ጃፋር በድሩ፣ ከሁለቱ ሀገራት የጥናትና ምርምር ተቋማት የተወከሉ ምሁራንና ባለሙያዎች በውይይቱ እየተሳተፉ መሆኑን ኢዜአ ዘግቧል፡፡