በክልሉ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥርና አስተዳደር አዋጅን ተፈፃሚ ለማድረግ ውይይት ተካሄደ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል የመኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥርና አስተዳደር አዋጅን ተግባራዊ በማድረግ አከራዮችና ተከራዮች መብትና ግዴታቸውን እንዲወጡ ማድረግ ያስፈልጋል ሲሉ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር ኢ/ር) ገለጹ፡፡
አዋጁን በተመለከተ ግንዛቤ ለማስጨበጥ በቦንጋ ከተማ በተካሄደ መድረክ ላይ ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር ኢ/ር)÷ አዋጁን በስድስቱ የዞን ዋና ከተሞች ተግባራዊ በማድረግ ተከራዮች እና አከራዮች መብትና ግዴታቸውን እንዲወጡ ማድረግ ያስፈልጋል ብለዋል።
አዋጁ የመኖሪያ ቤት አገልግሎትን የተረጋጋ ከማድረጉም ባለፈ የከተሞችን ገቢ ለማጎልበ ጭምር እንደሚረዳም መግለጻቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽ መረጃ ያመላክታል፡፡
አዋጁ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከፀደቀበት ከመጋቢት 24 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ተፈፃሚ የሆነ በመሆኑ የዞን አመራሮች ግንዛቤ በመፍጠር በታቀደው የጊዜ ገደብ እንዲተገበር መስራት እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡
በመድረኩ የክልሉ ካቢኔ አባላት፣ ምክትል ቢሮ ኃላፊዎች እንዲሁም የስድስቱ ዞን አመራሮችና የፍትህ መምሪያ ኃላፊዎች ተሳትፈዋል፡፡