Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር የሥራ ጊዜያቸውን አጠናቅቀው ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 28፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሥራ ጊዜያቸውን ያጠናቀቁት በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ዣኦ ዡዩአን ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል፡፡

የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደመላሽ ገ/ሚካኤል፣ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ እና ሌሎች አመራሮችም ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ተገኝተው አሸኛኘት አድርገውላቸዋል፡፡

በኢትዮጵያ የነበራቸው የሥራ ጊዜ ስኬታማ እንደነበር የገለጹት አምባሳደር ዣኦ ዡዩአን÷በሁለቱ ሀገራት ያለው ትብብር 50 ዓመታትን ከመሻገሩ ባለፈ ወደ ስትራቴጂያዊ አጋራነት ማደጉን ጠቅሰዋል።

አምባሳደሩ በኢትዮጵያ እና በቻይና መካከል ያለውን የሁለትዮሽ ግንኙነት ለማጠናከር ያደረጉት አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

በሥራ ቆይታቸው በቻይና መንግስት ድጋፍ በኢትዮጵያ እየተከናወኑ የነበሩ የተለያዩ የልማት ፕሮጀክቶች ለፍጻሜ መብቃታቸው ተጠቁሟል፡፡

ኢትዮጵያ ብሪክስን እንድትቀላቀል ቻይና ያደረገችው ድጋፍ የሁለቱ ሀገራት የረዥም ዘመን ጠንካራ ወዳጅነት ሌላኛው ማሳያ መሆኑም ተወስቷል።

በምንተስኖት ሙሉጌታ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.