Fana: At a Speed of Life!

በኦሮሚያ ክልል በ3 ሚሊየን ሄክታር ላይ የእንስሳት መኖ ለማልማት እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል በ3 ሚሊየን ሄክታር መሬት ላይ የእንስሳት መኖ ለማልማት እየተሰራ መሆኑን የክልሉ መስኖና አርብቶ አደር ልማት ቢሮ ገለጸ።

በኦሮሚያ ክልል ቆላማ አካባቢዎች እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ተግባራት የአርብቶ አደሩን ሕይወት እያሻሻሉ መሆኑ ተገልጿል፡፡

በክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ አስተባባሪነት የሚዲያ ሃላፊዎችና ባለሙያዎች በቦረና ዞን የአርብቶ አደሩን ሕይወት በዘላቂነት ለመቀየር እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎችን ጎብኝተዋል፡፡

የክልሉ የመስኖና አርብቶ አደር ልማት ቢሮ ም/ ሃላፊ አለሙ ረጋሳ (ኢ/ር) በዚህ ወቅት እንዳሉት÷የአርብቶ አደሩን ሕይወት ለማሻሻል ‘ፊና’ የተሰኘ የ25 ቢሊየን ብር ፕሮጀክቶች በክልሉ ቆላማ አካባቢዎች እየተተገበረ ነው፡፡

በቦረና ዞን 15 ፕሮጀክቶች እንደሚገኙ እና በኤልወዬ ወረዳ እየተገነባ ያለው አነስተኛ ግድብ መጎብኘቱንም ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ፕሮጀክቶቹ ለመስኖ፣ ለንጹህ መጠጥ ውሃ ፣ ለዓሳ እርባታ እና ለቱሪዝም ልማት ጭምር የሚውሉ መሆናቸው ተጠቁሟል፡፡

ዘንድሮ በመኖ ልማት ላይ በትኩረት በመሰራቱ በሰሪቴ ቀጠና ብቻ 10 ሚሊየን ብር የሚገመት 47 ሺህ እስር የሳር መኖ መከማቸቱ ተገልጿል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.