Fana: At a Speed of Life!

ከንቲባ አዳነች አቤቤ የነገዋ የሴቶች የተሀድሶና የክህሎት ማበልጸጊያ ማዕከል ሰልጣኞች ጋር የትንሳኤ በዓልን አከበሩ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 27፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ የነገዋ የሴቶች የተሀድሶና የክህሎት ማበልጸጊያ ማዕከል ሰልጣኞች ጋር የትንሳኤ በዓልን አክብረዋል፡፡

ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው÷ አዲስ አበባን እንደ ስሟ ውብ እና አበባ የማድረግ ስራችን አካል በሆነው የነገዋ የሴቶች የተሀድሶ እና የክህሎት ማበልጸጊያ ማዕከል ሰልጣኞች ጋር የትንሳኤ በዓልን አብረን አክብረናል ብለዋል፡፡

የትንሳኤ በዓልን አብረን ለማሳለፍ የጋበዝናቸው እንግዶች በማዕከሉ በስልጠና ላይ ለሚገኙ ለሁሉም እህቶቻችን የስራ እድል በመፍጠር አብረውን ለመስራት ቃል ገብተዋልም ሲሉ ገልጸዋል፡

“እነዚህን ልበ ቀና ባለሃብቶች በሰልጣኝ ሴት እህቶቻችን ስም ላመሰግናቸው እወዳለሁ” ያሉት ከንቲባዋ÷ አዲስ አበባችንን ማህበራዊ ፍትህ የነገሰባት የሁሉም ከተማ የማድረግ ስራችንን አጠናክረን እንቀጥላለን ብለዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.