Fana: At a Speed of Life!

የኢጋድ አባል ሀገራት የውሃ ሚኒስትሮች ጉባኤ ዛሬ መካሄድ ይጀምራል

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 29፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ድርጅት (ኢጋድ) አባል ሀገራት የውሃ ሚኒስትሮች ጉባኤ ዛሬ መካሄድ ይጀምራል፡፡

የኢጋድ አባል ሀገራት የውሃ ሚኒስትሮች ልዑካን በጉባኤ ለመሳተፍ በሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ የገቡ ሲሆን ፥ ጉባኤው በሸበሌ ወረዳ መካሄድ እንደሚጀምርም ነው የተገለጸው።

ለሁለት ቀናት ቆይታ በሚኖረው በዚህ ጉባኤ የሸበሌ ተፋሰስ ሀገራት የድንበር ተሻጋሪ የከርሰ ምድር ውሃ አጠቃቀም ዙሪያ ምክክር ይደረግበታል ተብሏል።

በጉባኤው የኢትዮጵያ፣ ጅቡቲ፣ ኬንያ፣ ኡጋንዳና ደብቡ ሱዳን ሀገራት የውሃ ሚኒስትሮዎች ጨምሮ የዓለም ባንክና ዩኒሴፍ ተወካዮች ተገኝተዋል፡፡

በጎህ ንጉሱ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.