Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ የፋይናንስ ተቋማት የብድር መጠን 2 ነጥብ 3 ትሪሊየን ብር ደረሰ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ የፋይናንስ ተቋማት የብድር መጠን 2 ነጥብ 3 ትሪሊየን ብር መድረሱን የብሔራዊ ባንክ ገዥ ማሞ ምህረቱ ተናገሩ።

በአይካፒታል አፍሪካ ኢንስቲትዩት ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር የተዘጋጀው 7ኛው የምስራቅ አፍሪካ አመታዊ የፋይናንስ ጉባኤ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው።

የብሔራዊ ባንክ ገዥ ማሞ ምህረቱ በጉባኤው መክፈቻ ላይ÷ ከምስራቅ አፍሪካ እንዲሁም በአህጉሩ ትስስርን ለመፍጠር፣ በዲጂታል ፍይናንስ፣ የተረጋጋ የፋይናንስ ዘርፍ ለመፍጠር፣ አካታችነት ላይ እየተከናወኑ ያሉ ተግባራትን ዘርዝረዋል።

የኢትዮጵያ የፋይናንስ ዘርፉ በተደራሽነት፣ በተቀማጭ ገንዘብ፣ በአጠቃላይ የሀብት መጠን ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መምጣቱን ተናግረዋል።

በፈረንጆቹ 2024 መጀመሪያ የፋይናንስ ተቋማት 121 መድረሳቸውን ጠቅሰው÷ አጠቃላይ ሀብታቸው ደግሞ 3 ነጥብ 4 ትሪሊየን እንዲሁም ተቀማጭ ገንዘባቸው 2 ነጥብ 4 ትሪሊየን ብር መድረሱን ገልጸዋል።

በተመሳሳይ የብድር መጠናቸውም 2 ነጥብ 3 ትሪሊየን ብር መድረሱን እንደገለጹ ኢዜአ ዘግቧል፡፡

መንግስት የተረጋጋ የፋይናንስ ዘርፍ ለመፍጠር ትኩረት መስጠቱን ያነሱት አቶ ማሞ ምህረቱ÷ በዚህም ጤናማ የፋይናንስ ዘርፍ ማስቀጠል ችሏል ብለዋል።

ዘርፉ ለውጭ ባለሀብቶች ክፍት መደረጉ ፈጠራና ውድድርን በማፍጠን መዋቅራዊ ለውጥ ለማምጣት አስተዋጽኦ እንዳለውም ገልጸዋል።

በዘርፉ የተደረገው የፖሊሲ ለውጥ የውጭ ኢንቨስተሮች ገብተው እንዲሰሩ በማድረግ አዲስ ካፒታል ለማምጣትና ዓለም አቀፍ ምርጥ ተሞክሮን ለመውሰድ እንደሚያስችልም አንስተዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.