Fana: At a Speed of Life!

የምርት ተወዳዳሪነት ላይ የሚመክር መድረክ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 2፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ የሚመረቱ ምርቶችን መጠንና ጥራት በመጨመር የምርት ተወዳዳሪነት መፍጠር ላይ የሚመክር መድረክ እየተካሄደ ነው

በኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አዘጋጅነት ከግንቦት 1 እስከ 5 ቀን 2016 ዓ.ም በሚሊኒየም አዳራሽ የሚካሄደው የኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ እንደቀጠለ ነው።

የኤክስፖው አካል የሆነ የፓናል ውይይት እየተካሄደ ሲሆን በመድረኩ የምርት ተወዳዳሪነት ላይ ውይይት እየተደረገ ይገኛል።

96 ምርቶች ተለይተው ለማምረት እንደ ሀገር ዝግጅት በመደረግ ላይ እንደሆነ በመድረኩ ተነስቷል።

ምርትን በማሳደግና ተወዳዳሪነትን በመጨመር ለውጭ ገበያ ምርትን በስፋት ማቅረብ እንደሚያስፈልግ ተነስቷል።

በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ ለመሆን ምን እየተሰራ እንደሆነም በውይይቱ የተነሳ ሲሆን፤ በዋናነት የሀገር ውስጥ ምርትና ተኪ ምርት፣ የሀገር ውስጥ ምርት ጥራት፣ በሀገር ውስጥ ምርት ስለ መኩራት እና በብራዲንግ ምንነት ላይ ውይይት እየተደረገ ነው፡፡

በመድረኩ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል፣ የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትር ገ/መስቀል ጫላ እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል፡፡

በፈትያ አብደላ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.