Fana: At a Speed of Life!

4ኛው ሀገር አቀፍ የምርምር ኮንፈረንስ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 2፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) 4ኛው ሀገር አቀፍ የምርምር ኮንፈረንስ “ምርምር ለዘላቂ ኑሮ”በሚል መሪ ሀሳብ በቦንጋ ዩኒቨርሲቲ እየተካሄደ ነው።

በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ሀብት ልማት የስራና ቴክኖሎጂ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ነገሪ ሌንጮ (ዶ/ር) እና የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ጴጥሮስ ወ/ጊዮርጊስን (ዶ/ር) ጨምሮ የተለያዩ እንግዶች በኮንፈረንሱ እየተሳተፉ ነው፡፡

በኮንፈረንሱ የተለያዩ ችግር ፈቺ የምርምር ስራዎች ቀርበው ውይይት ይደረግባቸዋል ተብሎ ይጠበቃል።

በተመሳሳይ በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ 12ኛው ዓመታዊ የጥናት እና ምርምር ኮንፈረንስ “በቴክኖሎጂ የታገዘ ጥናትና ምርምር ለሁለንተናዊ ዕድገት” በሚል መሪ ሃሳብ እየተካሄደ ነው።

 

በመድረኩ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ጉቼ ጉሌ (ዶ/ር)÷ ለሀገር ሁለንተናዊ ዕድገትና ለውጥ በቴክኖሎጂ የታገዘ ጥናትና ምርምር እንዲሁም ዘመናዊ ኢኖቬሽን ፖሊሲ መጠቀም ወሳኝ ነው ብለዋል::

እንደ ሀገር የተፈጥሮ ፀጋዎች በአግባቡ ለመጠቀም በቴክኖሎጂ የታገዘ ጥናትና ምርምር ፋይዳው የጎላ ነው ሲሉም ገልፀዋል::

በኮንፈረንሱ የተገኙት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ይሽሩን አለማየሁ (ዶ/ር)÷ በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ የታገዙ የምርምር ስራዎች ከዩኒቨርሲቲዎች ጋር በመሆን እየተከናወኑ እንደሆነ ጠቁመዋል።

በወንድሙ አዱኛ እና በዮሴፍ ጩሩቆ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.