Fana: At a Speed of Life!

የኦሮሚያና የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልሎች በሰላምና ጸጥታ ዙሪያ እየመከሩ ነው

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 2፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ እና የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልሎች በአዋሳኝ አካባቢዎች ሰላምና ጸጥታ ዙሪያ በወሊሶ ከተማ እየመከሩ ነው።

በውይይታቸውም ቀደም ሲል ሁለቱ ክልሎች የሰላምና ጸጥታ መዋቅር ተወካዮች በቡታጅራ ከተማ ተገኝተው የመከሩባቸውን ጉዳዮችና ያስቀመጧቸውን የጋራ አቅጣጫዎች እየገመገሙ ነው፡፡

በተጨማሪም በቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ እየመከሩ እንደሚገኙ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በውይይቱ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሰላምና ጽጥታ ቢሮ ኃላፊ ተመስገን ካሳ፣ የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽነር ሽመልስ ካሳ፣ የኦሮሚያ ክልል አስተዳደርና ጸጥታ ቢሮ ምክትል ኃላፊ ሀይሌ ጉርሜሳ እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.