Fana: At a Speed of Life!

230 ኢትዮጵያውያን ከኦማን ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 2፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) 230 ኢትዮጵያውያን ከኦማን ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል፡፡

ወደ ሀገር ቤት የተመለሱት ዜጎች ሁሉም ወንዶች መሆናቸው ተገልጿል፡፡

ለተመላሽ ዜጎች በአየር ማረፊያና በማቆያ ማዕከላት ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ በማድረግ ከቤተሰብ ጋር የመቀላቀል ስራ እየተሰራ እንደሚገኝም ተጠቁሟል፡፡

ከሚያዝያ 29 ቀን 2016ዓ.ም ጀምሮ እየተከናወነ በሚገኘው ከኦማን ዜጎችን ወደ ሀገር የመመለስ ስራ 460 ኢትዮጵያውያንን መመለስ መቻሉን የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል፡፡

በኦማን የሚገኙ 1 ሺህ 590 ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገር ለመመለስ መታቀዱ የሚታወስ ነው።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.