Fana: At a Speed of Life!

ለአማራ ክልል 25 ሚሊየን ብር የሚያወጡ የኮንፈረንስ ካሜራዎች ድጋፍ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 2፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ለአማራ ክልል 25 ሚሊየን ብር የሚያወጡ 43 የቪዲዮ ኮንፈረንስ ካሜራዎች ድጋፍ አድርጓል፡፡

ድጋፉ በክልሉ የሚከናወኑ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ዘርፍ ሥራዎችን በማጠናከር ውጤታማ ለማድረግ ያለመ ነው ተብሏል።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ/ር)÷ በክልሎች የሚከናወኑ የዘርፉን ሥራዎች ለማጠናከር የቁሳቁስ፣ የአቅም ግንባታ እና የመሰረተ ልማት ዝርጋታ ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የቪድዮ ኮንፈረንስ ካሜራ ድጋፉ ለሁሉም ክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች ተደራሽ መደረጉንም ነው ያስገነዘቡት፡፡

በቀጣይ በክልሎች በድጋፍ የሚሰሩ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂና የዲጂታላይዜሽን ስራዎችን ለማጠናከር ፕሮጀክቶችን በመንደፍ እንደሚሰራ መናገራቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

በአማራ ክልል በም/ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የከተማ ክላስተር አስተባባሪና የከተሞችና መሰረተ ልማት ቢሮ ሃላፊ አህመዲን መሃመድ (ዶ/ር)÷ ድጋፉ በክልሉ ከተሞች የሚሰሩ ሥራዎችን ለማጠናከር ይረዳል ብለዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.