Fana: At a Speed of Life!

የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ አባላት ባሕር ዳር ገቡ

 

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 2፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ አባላት ባሕር ዳር ከተማ ገብተዋል።

በዚህም የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት እና የዋና ጽሕፈት ቤት ኀላፊ አደም ፋራህ፣ የክልሎች ርእሳነ መሥተዳድሮች፣ ሚኒስትሮች እና ሌሎችም የፓርቲው ሥራ አሥፈጻሚ አባላት ባሕር ዳር ከተማ ገብተዋል።

አባላቱ በባሕር ዳር ደጃዝማች በላይ ዘለቀ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርሱ የአማራ ክልል ከፍተኛ መሪዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች እና ሌሎችም የከተማው ነዋሪዎች አቀባበል እንዳደረጉላቸው አሚኮ ዘግቧል፡፡

ሥራ አስፈጻሚ አባላቱ በአማራ ክልል በሚኖራቸው ቆይታ በክልሉ የሚከናወኑ የልማት ሥራዎችን እና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮችን እንደሚመለከቱ ይጠበቃል።

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.