በኢትዮጵያ የዘረ-መል ምርመራ አገልግሎት መስጠት ሊጀመር መሆኑ ተገለጸ
አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 1 ፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በውጭ ሀገራት ይደረጉ የነበሩ የዘረ-መል ምርምራዎችን በሀገር ውስጥ ለማካሄድ ቅድመ ዝግጅት እተደረገ ነው።
ከአሁን ቀደም የሰው እና የዕፅዋት ዘረ-መል ምርመራ ለማድግ የሚያስችል አቅም ሀገር ውስጥ ስላልነበረ ኢትዮጵውያን ተመራማሪዎች ስራዎቻቸውን ወደ ውጭ በመላክ ለማስመርመር ይገደዱ ነበር።
የኢትዮጵያ ባዮ ቴክኖሎጂ ኢንስቲቲዩት የዘር-መል ምርመራን በሀገር ውስጥ ለማድረግ የሚያስችለውን መሳሪያ “አሊያንስ ግሎባል ግሩፕ”ከተሰኘ ድርጅት በድጋፍ መልክ ማግኘቱን አስታውቋል።
በዚህ መሰረትም በቀጣይ ምርመራው በሀገር ወስጥ የሚከናወን መሆኑ ነው የተገለጸው።
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ጀማል በከር የዘረ-መል ምርመራ ሀገር ውስጥ ለማድረግ የሚያስችል አቅም መፈጠሩ የሀገር ውስጥ ተመራማሪዎችን ወጪና ድካም እንደሚቀንስና በዘርፉ የሚደረገውን ምርምር እንደሚያነቃቃው ተናግረዋል።
የተለያዩ ተቋማትና ግለሰቦች የዘረ-መል ምርመራ ለማድረግ የሚያወጡትን ወጪ በመቀነስ የውጭ ምንዛሬ ፍለጋንም እንደሚያስቀር አብራርተዋል።
ስምምነቱን የኢትዮጵያ ባዮ ቴክኖሎጂ ኢንስቲቲዩት ዳይሬክተር ጀነራል ዶክተር ካሳሁን ተስፋየ (ዶ/ር) እና “የአሊያስ ግሎባል ግሩፕ” ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶክተር ታመር ድግዲ ተፈራርመዋል።
የዘረ-መል ምርመራ ማድረጊያ መሳሪያው ለምርመራ ወደ ውጭ የሚላኩ ዘረ-መሎች (የሠው፣ የእንስሳትና የዕፅዋት) የመሰረቅ አደጋ እንዳይገጥማቸው የነበረውን ስጋት እንደሚቀርፍ ተገልጧል።
የ‹‹አሊያንስ ግሎባል ግሩፕ›› 17ኛ ቢሮውን “አሊያስ ግሎባል ግሩፕ አቢሲኒያ” በሚል አዲስ አበባ መክፈቱን ከኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።