የጃፓኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ሺንዞ አቤ ስልጣን መልቀቃቸውን አስታወቁ
አዲስ አበባ፤ ነሀሴ 22 ፣2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የጃፓኑ ጠቅላይሚኒስትር ሺንዞ አቤ ከጤና እክል ጋር በተያያዘ ስልጣን መልቀቃቸውን አስታወቁ።
የ65 ዓመቱ አቤ ያጋጠማቸው የጤና እክል በመንግስታቸው ስራ ላይ እንቅፋት እንዳይፈጥር መልቀቃቸውን በዛሬው ዕለት ገልፀዋል።
ከስልጣኔ በመልቀቄ ከልብ ይቅርታ እጠይቃለሁ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ውሳኔያቸው በጃፓን የውስጥ ፓለቲካ ላይ ችግር ሊፈጥር እንደማይገባ ተናግረዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተለይም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የጤናቸው ሁኔታ አሳሳቢ እየሆነ መምጣቱም ነው የተነገረው፡፡
አቤ ጃፓንን ለረጅም ጊዜ በጠቅላይ ሚኒስትርነት በመምራት ቀዳሚ ናቸው፡፡
የጃፓን መገነኛ ብዙሃን አዲስ ጠቅላይ ሚኒስትር እስከ ሚሾም አቤ በጠቅላይ ሚኒስትርነታቸው እንደሚቀጥሉ የዘገቡ ሲሆን ይህም ጊዜያዊ ጠቅላይ ሚኒስትር መሾምን ያስቀራል ብሏል አር ቲ በዘገባው።