ባለፉት 24 ሰዓታት 1 ሺህ 105 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው፤ የ18 ሰዎች ሕይወት አልፏል
አዲስ አበባ፣ ነሀሴ 27፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 21 ሺህ 360 የላብራቶሪ ምርመራ 1 ሺህ 105 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።
በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 54 ሺህ 409 መድረሱንም ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ በፌስቡክ ገፃቸው ያወጡት መረጃ ያመለክታል።
ከዚህ ባለፈ የ18 ሰዎች ህይወት በቫይረሱ ምክንያት ያለፈ ሲሆን፥ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ በቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 846 መድረሱንም አመላክተዋል።
በትናንትናው እለት 416 ሰዎች ከኮሮና ቫይረስ ያገገሙ ሲሆን፥ 303 ሰዎች ፅኑ ህሙማን የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል።
በአጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 19 ሺህ 903 መድረሱን ሚኒስትሯ ገልፀዋል።