የትግራይ ክልል መንግስት በአፋር ክልል በጎርፍ ምክንያት ለተፈናቀሉ ዜጎች ድጋፍ አደረገ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 7፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በአፋር ክልል በጎርፍ ኣደጋ ምክንያት ከመኖሪያቸው ለተፈናቀሉ ዜጎች የተለያዩ ድጋፎችን አደረገ።
የክልሉ መንግስት በጎርፍ ምክንያት ለተፈናቀሉ ዜጎች ያደረገው ከ5 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመቱ የተለያዩ የምግብ ግብአቶችና ቁሳቁሶች ድጋፍ ማድረጉን የክልሉ ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ አስታውቋል።
#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።