Fana: At a Speed of Life!

የአልጄሪያው ፕሬዚዳንት ሆስፒታል ገቡ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 18፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ወሳኝ የህገ መንግስት ህዝበ ውሳኔ ለማድረግ ዝግጅት ላይ የምትገኘው አልጀሪያ ፕሬዚዳንት አብደልማጂድ ቴቦኔ ሆስፒታል ገቡ።
 
ፕሬዚዳንቱ ሀገራቸው ወሳኝ የሚባለውን ህገ መንግስታዊ ህዝበ ውሳኔ ለማድረግ ቀናት በቀራት ወቅት በዋና ከተማዋ አልጀርስ ወደሚገኝ ወታደራዊ ሆስፒታል ገብተዋል።
 
የፕሬዚዳንቱ በርካታ የቅርብ ደጋፊዎች እና የመንግስት ባለስልጣናት የኮሮና ቫይረስ ከተገኘባቸው በኋላ በዶክተሮቻቸው ምክር ለአምስት ቀናት ራሳቸውን አግልለው ቆይተዋል።
 
አሁን ላይ ፕሬዚዳንቱ በልዩ ክፍል በጥሩ ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ያስታወቀው የፕሬዚዳንቱ ቢሮ ስራቸውን መስራት እንደሚቀጥሉም ገልጿል።
 
በመጭው እሁድ በአልጀሪያ የፕሬዚዳንቱን የስልጣን ጊዜ ለመገደብ፣ ፓርላማው እና ፍርድ ቤት ተጨማሪ ስልጣን እንዲያገኙ የሚያደርግ የህገ መንግስት ማሻሻያ ለማድረግ ህዝበ ውሳኔ ይደረጋል።
 
ምንጭ፦ ቢቢሲ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.