Fana: At a Speed of Life!

የሲዳማ ክልል ለመከላከያ ሰራዊት 240 የእርድ ሰንጋ እና 107 በጎችና ፍየሎች ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 11፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ለጀግናው የሀገር መከላከያ ሰራዊት 240 የእርድ ሰንጋና 107 በጎችና ፍየሎች ድጋፍ ማድረጉን የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ ገለጹ።

ርዕሰ መስተዳድሩ መንግስት ተገዶ የገባበትን ህግ የማስከበር እርምጃ የሲዳማ ክልል ህዝብ እንደሚደግፍና ከጀግናው መከላካያ ሰራዊት ጎን እንደሚቆምም ገልጸዋል፡፡

በቀጣይም ድጋፉ ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን ነው አቶ ደስታ የተናገሩት፡፡

አቶ ደስታ መላው የክልሉ ህዝብ ለጀግናው መከላከያ ሰራዊት በደማቅ ሁኔታ የሞራል ድጋፍ ሲያደርግ መቆየቱን አስታውሰዋል፡፡

የክልሉ ህዝብ እስካሁን ላበረከተው አስተዋፅኦ ያላቸውን አክብሮትና አድናቆትም ገልጸዋል።

የህወሓት ቡድን እኔ ካልመራሁ ሀገር ይፍረስ የሚል ተራ እሳቤ በመያዝ ላለፉት 27 ዓመታት የፈፀሙትን ሀገርን የመዝረፍ ተግባር ለመድገም ፍላጎት ቢኖራቸውም አልተሳካላቸውም ብለዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.