Fana: At a Speed of Life!

የፖለቲካ ፓርቲዎችና የግል እጩ ተወዳዳሪዎች የመገናኛ ብዙሃን ድልድል ረቂቅ መመሪያ ላይ ውይይት ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 11፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ በስድስተኛው ሀገራዊ ምርጫ የፖለቲካ ፓርቲዎችና የግል እጩ ተወዳዳሪዎች የመገናኛ ብዙሃን ድልድል ረቂቅ መመሪያ ላይ ከመገናኛ ብዙሃንና ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ተወያየ።

የውይይቱ ዓላማ ዕጩ ተወዳዳሪዎች ቀደም ሲል በተካሄዱ ምርጫዎች በመገናኛ ብዙሃን ቅስቀሳ ሲያቀርቡ ያጋጠማቸውን ችግሮች በማንሳት ለስድስተኛው ሀገራዊ ምርጫ ፍትሃዊና ሚዛናዊ አሰራር ለመዘርጋት ነው ተብሏል።

ረቂቅ መመሪያው ለመድረኩ ተሳታፊዎች ቀርቦ አስተያየት እንደተሰበሰበ ኢዜአ ዘግቧል።

ምርጫ ቦርድ በሚያወጣው መመሪያና በሚወስነው የድልድል መስፈርት መሰረት ድልድሉ በሶፍትዌር በመታገዝ እንደሚከፋፈልም ተገልጿል።

በዛሬው መድረክ የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን የአሰራር ስርዓት ላይ ማብራሪያ ተሰጥቷል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.