13 የህወሓት የጥፋት ተላላኪዎች በኦሮሚያ ክልል ቦረና ዞን በቁጥጥር ስር ዋሉ
አዲስ አበባ ፣ ህዳር 16 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ጥፋት ሊያደርሱ ዝግጅት ላይ የነበሩ 13 የህወሓት ተላላኪዎች በቦረና ዞን በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገለፀ፡፡
ተጠርጣሪዎቹ በቦረና ዞን ጎሞሌ ወረዳ በተደረገ ድንገተኛ ፍተሻ እና የህብረተሰብ ጥቆማ ነው በቁጥጥር ስር የዋሉት ተብሏል፡፡
የዞኑ ኮሙኒኬሽን ፅህፈት ቤት እንዳስታወቀው ተጠርጣሪዎቹን ጥፋት ሳያደርሱ ቀድሞ መያዝ ተችሏል፡፡
ተጠርጣሪዎቹ የህወሓት ጁንታ የጥፋት ተላላኪዎች መሆናቸውን የወረዳው ፖሊስ ፅህፈት ቤት ገልፆ፣ በህብረተሰቡ የነቃ ተሳትፎ ጉዳት ሳያደርሱ በቁጥጥር መዋላቸውን አስታውቋል፡፡
ፖሊስ የአካባቢውን ፀጥታ ለማስጠበቅ ከነዋሪዎች ጋር በትብብር እየሰራ መሆኑንም ገልጿል፡፡