አቶ ደመቀ መኮንን ከአፍሪካ ብሔራዊ ኦሊምፒክ ኮሚቴዎች ማህበር ፕሬዚዳንት ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ ፣ ህዳር 25 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከአፍሪካ ብሔራዊ ኦሊምፒክ ኮሚቴዎች ማህበር (አኖካ) ፕሬዚዳንት ሙስጠፋ ቤራፍ ጋር ተወያዩ፡፡
በመጭው እሁድ በአዲስ አበባ በሚካሄደው የአፍሪካ ብሔራዊ ኦሊምፒክ ኮሚቴዎች ማህበር (አኖካ) ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ፕሬዚደንቱ አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡
በውይይቱ አቶ ደመቀ በክልል ከተሞች ስታዲየሞች እና የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች መገንባታቸውን በመጥቀስ ዓለም አቀፍ የስፖርት ውድድሮችን የማስተናገድ አቅም እንዳላቸው ገልፀዋል፡፡
የማህበሩ ፕሬዚዳንት ሙስጠፋ ቤራፍ በበኩላቸው ለተደረገላቸው ገላፃ አመስግነው አኖካ በኢትዮጵያ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅርበት መስራቱን እንደሚቀጥል ተናግረዋል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል
https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!