ቅዳሜና እሁድ ለሕጻናት ነፃ የዓይን ሕክምና አገልግሎት እንደሚሰጥ የቅዱስ ጳውሎስ ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ አስታወቀ
አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 9፣ 2013 (ኤፍቢሲ) የቅዱስ ጳውሎስ ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ ቅዳሜና እሁድ ለሁለት ተከታታይ ቀናት ለሕጻናት ነፃ የዓይን ሕክምና አገልግሎት እንደሚሰጥ አስታወቀ፡፡
ህክምናው የሚሰጠው በመድሃኒት፣ በመነጽር ህክምና ወይም በቀዶ ጥገና መፍትሄ ማግኘት ላልቻሉ ሕጻናት ብቻ መሆኑንም ገልጿል፡፡
ህክምናው ዓይነ ስውርነትንና የዕይታ ችግሮችን ለመከላከል የተዘጋጀ ልዩ የነጻ ምርመራ ፕሮግራም ነው።
ወላጆችና አሳዳጊዎች በተጠቀሰው የዕድሜ ክልል ያሉ ምንም ዓይነት የዓይን ምርመራ አድርገው የማያውቁ ወይም ችግር ኖሮባቸው ህክምና ያላገኙ ልጆቻቸውን ይዘው እዲመጡ ጥሪ አቅርቧል፡፡
ምርመራው የዕይታ ችግርን፡ ዓይነ ስውርነትን እንዲሁም የልጆችን ዕይታ ለማስተካከል ያለመ መሆኑን ነው የገለጸው፡፡
ይህ ፕሮግራም ከዚህ በፊት ህክምና ሲያገኙ የነበሩና ክትትል እየተደረገላቸው የሚገኙ ልጆችን እንደማያካትት ከቅዱስ ጳውሎስ ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!