Fana: At a Speed of Life!

የፌደራል ተቋማት አስተባባሪ ኮሚቴ በወቅታዊ ሃገራዊ ጉዳዮች ላይ ተወያየ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 14 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌደራል ተቋማት አስተባባሪ ኮሚቴ በወቅታዊ ሃገራዊ ጉዳዮች ላይ ተወያየ፡፡

በውይይቱ ላይ የልዩ ልዩ ተቋማት ሚኒስትሮች፣ ሚኒስትር ዲኤታዎች እና በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ሹመት የተሰጣቸው ዳይሬክተሮች፣ ምክትል ዳይሬክተሮች እንዲሁም ኮሚሽነሮችና ምክትል ኮሚሽነሮች ተገኝተዋል፡፡

በወቅታዊ ሃገራዊ ፖለቲካዊ ሁኔታዎችና የቀጣይ ትኩረት አቅጣጫዎች፣የብልጽግና ስኬቶችና ቀጣይነት ያለው ትግል የሚሹ አዝማማያዎች እንዲሁም ፓርቲውን ከውስጥና ከውጭ እያጋጠሙ ያሉ ወቅታዊ ተግዳሮቶችን በሚመለከት ውይይት ተደርጓል፡፡

ሃገራዊ ድሉ የጋራ ድል በመሆኑ ሳንኩራራ ለቀጣይ ድል ራስን በማዘጋጀት ህብረ ብሔራዊ አንድነትን በመጠበቅ የተገኘውን ውጤት ለሀገር ግንባታ ማዋል እንደሚገባ የጋራ መግባባት ላይ መደረሱን ከብልፅግና ፓርቲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.