Fana: At a Speed of Life!

የእንግሊዝ ፓርላማ ብሪታንያ ከአውሮፓ ህብረት ጋር የደረሰችውን የንግድ ስምምነት በአብላጫ ድምጽ አጸደቀ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 22፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በብሪታንያና በአውሮፓ ህብረት መካከል የተደረሰው የንግድ ስምምነት ከዛሬ ጀምሮ ተግባራዊ መሆን ይጀምራል፡፡

ህብረቱ ከሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን አስተዳደር ጋር መስማማቱን ተከትሎ በትናንትናው ዕለት የብሪታንያ የህዝብ ተወካዮች አባላት ስምምነቱን በአብላጫ ድምጽ አጽድቀውታል፡፡

ቦሪስ ጆንሰን የፓርላማ አባላቱ 521 በሆነ የድጋፍ እና በ73 ተቃውሞ በአብላጫ ድምጽ ስምምነቱን መቀበላቸውን አመስግነው እጣ ፈንታችንን በእጃችን አስገብተናል ብለዋል፡፡

በህብረቱ በኩል የአውሮፓ ኮሚሽን ፕሬዚዳንት ኦርሱላ ቮን ደር ሌየን እና የአውሮፓ ህብረት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ቻርለሰ ሚሼል በብራሰልስ የንግድ ስምምነቱ ላይ ፊርማቸውን አኑረዋል፡፡

ዛሬ ተግባራዊ መሆን የሚጀምረው የንግድ ስምምነት ብሪታንያን ከህብረቱ የጋራ ገበያ እና ከጉሙሩክ ማህበሩ ያስወጣታል፡፡

በአንጻሩ ግን ከህብረቱ ጋር በሚኖራት የንግድ ልውውጥ በሸቀጦች ላይ ቀረጥን አይጥልም፤ ይህም በብሪታኒያውያን ዘንድ የነበረውን ስጋት የቀረፈ ነው፡፡

ብሪታንያውያን ከህብረቱ ለመውጣት ድምጽ የሰጡት በ2016 ሲሆን በ2020 የመጀመሪያው ወር ላይ የንግድ ስምምነቱን በይደር አቆይተው ከህብረቱ መውጣታቸው የሚታወስ ነው፡፡

በይደር የሰነበተው ስምምነትም መቋጫ አግኝቶ በአውሮፓውያን አዲስ ዓመት ዋዜማ ብሪታንያ እና ህብረቱ ተስማምተዋል፡፡

 

ምንጭ፡-ቢቢሲ

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.