Fana: At a Speed of Life!

አሜሪካ ብሪታኒያ የሁዋዌን አምስተኛ ትውልድ ኔትወርክን (5G) እንዳትጠቀም አሳሰበች

አዲስ አበባ፣ ጥር 5፣ 2012(ኤፍ ቢሲ) አሜሪካ የሁዋዌ የአምስተኛ ትውልድ ኔትወርክን (5G) መጠቀም እብደት ነው ስትል ብሪታኒያን አስጠነቀቀች፡፡

አሜሪካ  የቻይና ኩባንያዎች አገልግሎት መጠቀም ሊያስከትል የሚችለውን የደህንነት ስጋት የሚያሳይ  አዲስ ማስረጃ ለብሪታኒያ አቅርባለች፡፡

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በጉዳዩ ዙሪያ በሀገሪቱ  ጠቅላይ  ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ላይ ጫና ለማሳደር እንደሚፈልጉ ተጠቁሟል፡፡

በዚህ ወር ሁዋዌ ኩባንያ ለብሪታኒያ የኔትወርክ ዝርጋት አንዳንድ “መሠረታዊ ያልሆኑ” ክፍሎችን ያቀርብ አያቅርብ የሚል ውሳኔ ይተላለፋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

የሁዋዌ ቃል አቀባይ ባለፉት 15 ዓመታት ለብሪታኒያ የ3ጂ ፣ 4ጂ እና ብሮድባንድ መሳሪያዎችን  ሲያቀርብ የቆየ የግል ኩባንያ መሆኑን በመግለፅ በዚህም የሃገሪቱ ባለሙያዎች ቴክኖሎጂያቸው የደህንነት ስጋት እንደማያመጣ ማረጋገጣቸውን ጠቁመዋል፡፡

አሜሪካ ባለፈው ዓመት በደህንነት ስጋት ምክንያት ለሁዋዌ እና 68 ተዛማጅ ኩባንያዎች የቴክኖሎጂና ሌሎች መሳሪያዎችን እንዳይሸጡ ገደብ መጣሏ የሚታወስ ነው፡፡

ምንጭ፡-ቢቢሲ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.