Fana: At a Speed of Life!

ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ለጥምቀት በዓል ጎንደር ገቡ

አዲስ አበባ፣ ጥር 10፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ)  የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ለጥምቀት በዓል ጎንደር ከተማ ገቡ።

ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ጎንደር ሲደርሱም የአማራ ክልል ከፍተኛ ባለስልጣናት አቀባበል አድርገውላቸዋል።

በተመሳሳይ ቀዳማዊት እመቤት ወይዘሮ ዝናሽ ታያቸው ለበዓሉ ጎንደር ገብተዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማም በተመሳሳይ ለበዓሉ ከተማዋ ደርሰዋል።

በጎንደር ዛሬ የከተራ በዓል ነገ ደግሞ የጥምቀት በዓል በድምቀት ይከበራል።

ለበዓሉ ከተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች እና የውጭ ሀገራት ጎንደር ከተማ በመግባት ላይ ይገኛሉ።

ዛሬ ማለዳ ላይም ቁጥራቸው ከፍ ያለ የውጭ ሀገራት ቱሪስቶች በበዓሉ ላይ ለመታደም ጎንደር ገብተዋል።

የጥምቀት በዓልም በተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) የማይዳሰስ ቅርስ ሆኖ ዘንድሮ መመዝገቡ ይታወሳል።

 

በሶዶ ለማ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.