የዶናልድ ትራምፕ ፌስቡክ ገፅ ታገደ
አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 27 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌስቡክ ኩባንያ የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕን የግል ፌስቡክ እና ኢንስታግራም ገፆች ለሁለት ዓመት አገደ፡፡
ፌስቡክ ትራምፕን ያገደው የኩባንያውን ደንብ በመጣስ በአሜሪካ ምክር ቤት (ካፒታል ሂል) ላይ የተፈፀመውን ጥቃት አበረታተዋል በሚል ነው፡፡
እገዳውም ካሳለፍነው የፈረንጆቹ ጥር ወር ጀምሮ ታሳቢ የሚደረግ ነው ተብሏል፡፡
በዚህም እገዳው ለሚቀጥሉት ሁለት ዓመትታ የሚቆይ መሆኑ ታውቋል፡፡
ምንጭ፡-ቢቢሲ