የቀበሌ ቤቶች ባሉበት አካባቢ ነዋሪዎቹ ሳይነሱ የቤት ማልማት ስትራቴጂ ሊተገበር ነው
አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 7፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የቀበሌ ቤቶች ባሉበት አካባቢ ነዋሪዎቹ ሳይነሱ የቤት ማልማት ስትራቴጂ እንደሚተገበር የአዲስ አበባ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ አስታወቀ።
በቢሮው አማራጭ የቤት ልማት አቅርቦት ዳይሬክተር አቶ ጳውሎስ ታምራት እንደገለፁት መልሶ ማልማት ላይ ነዋሪዎችን ወደ ሌላ ቦታ በማዘዋወር ይከናወን የነበረው የቤት ልማት ፕሮግራምን በመቀየር ወደ አብሮ መልማት በማሻሻል ማህበረሰቡ ባለበት ቦታ ቤቱን እና አካባቢውን ዘመናዊ የማድረግ ሥራ ይሰራል።
ግንባታ ሲካሄድ ብቻ ባለሃብቱ ወይም መንግስት የአካባቢውን ነዋሪ ለተወሰነ ጊዜ በኪራይ የተለያየ ቦታ አቆይቶ ግንባታው ሲጠናቀቅ መልሶ በዛው በነበሩበት አካባቢ ቤት አግኝተው እንዲኖሩ እንደሚደረግ ጠቁመዋል።
አብሮ መልማት ነዋሪው ሳይፈናቀል ባለበት እንዲቆይ እና ያለው ማህበራዊ ግንኙነት ሳይፋለስ የሚተገበር ነው ማለታቸውን ኢፕድ ዘግቧል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!