በመንገድ ደህንነት የሁለተኛ ዲግሪ ትምህርት ሊጀመር ነው
አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 8፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የመንገድ ደህንነት ትምህረት የሁለተኛ ዲግሪ ትምህርት ማስጀመሪያ መርሃግበር እየተካሄደ ነው።
የትራንስፓርት ሚኒስትሯ ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ ፣ እና የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝደንት ፕሮፌሰር ጣሰው ወልደሃና በተገኙበት ነው መርሃግብሩ የተካሄደው።
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መስጠት በሚጀምረው ትምህርት ለመንገድ ደህነንትና አሳሳቢ የሆነውን የትራፊክ አደጋ መቀነስ ሚና የሚኖራቸው ይዘቶች እንደሚካተቱ ተገልጿል።
ከየክልሉ የተመረጡ 25 ተማሪዎችም በመጀመሪያው ዙር የሚማሩ ሲሆን÷ በቀጣይም በርካታ የዘርፉ ባለሙያዎችን አሰልጥኖ ለማውጣት መሰረት የሚጥል ነው ተብሏል።
የትራንስፓርት ሚኒስትሯ ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ÷በአገራችን ኢትዮጵያ የመንገድ ደህንነት ጉዳይ ላይ በተለይም በትራፊክ አደጋ በዛ ያሉ ዜጎቻችን የምናጣበት በርካታ ምክንያቶች ተጠቃሾች ሲሆኑ÷ ከእነዚህ ውስጥ አንዱ በዘርፉ ብቃት ያለው ባለሙያ በሚፈለገው ደረጃ አለመገኘትና አጠቃላይ በዘርፉ እንደ አገር ያለን የሰለጠነ የሰው ሃይል እጥረት አንዱና ዋነኛው መሆኑን አንስተዋል።
የመንገድ ደህንነት ስራን እንደ ዋነኛ ስርዓት ሊመራ፣ ሊያስተባብር እና ቀጣይነት ባለው መልኩ አጠናክሮ የሚሄድ የሰለጠነ የሰው ሃይል መኖር በአገራችን በመንገድ ትራፊክ አደጋ ምክንያት የሚደርሰውን የሞት ምጣኔ በ10 ሺህ ተሽከርካሪዎች በ2012 ከነበረበት 34 ነጥብ 4 በ2022 ዓ.ም ወደ 10 ዝቅ ለማድረግ ያስቀመጥነውን እቅድ ወደ ውጤት ለመቀየር፣ ትምህርት ቁልፍ መሳሪያ መሆኑን ተገንዝበናል ብለዋል።
የትራንስፖርት ሚኒስቴር ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመሆን የመንገድ ደህንነት ስርአት በካሪኩለም ውስጥ ተካቶ ከ2014 ዓ.ም ትምህርት ዘመን ጀምሮ ለተማሪዎች ሊሰጥ መሆኑ ይታወቃል።
ኢትዮጵያ ከዚህ ቀደም በመንገድ ትራፊክ ደህነነት ዙሪያ ባለሙያዎችን ከውጭ ሀገራት በማስመጣት ስታሰራ መቆየቷ ከሚኒስቴሩ የተገኘ መረጃ ያመለክታል።
በዩኒቨርሲቲው የመንገድ ትራፊክ ደህነንት ጋር በተገናኘ የሚሰራ የልህቀት ማእከል የማቋቋም ውጥን ስለመኖሩም ተነስቷል።
በተጨማሪም የትራንስፓርት ሚኒስቴርና የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በዘርፉ አብረው መስራት የሚያስችላቸውን የመግበባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል።
በሀብታሙ ተ/ስላሴ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
0
People Reached
0
Engagements
Boost Post
Like
Comment
Share