Fana: At a Speed of Life!

ለመጪው ምርጫ ድምጽ ለመስጠት መዘጋጀታቸውን የቻግኒ ከተማ ነዋሪዎች ተናገሩ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 11፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ሰኞ ለሚካሄደው ሀገር አቀፍ ምርጫ ድምጻቸውን ለመስጠት መዘጋጀታቸውን የቻግኒ ከተማ ነዋሪዎች ተናግረዋል።
በቻግኒ የምርጫ ክልል በአጠቃላይ 72 የምርጫ ጣቢያዎች መኖራቸውንና ከ49 ሺህ በላይ መራጮች መመዝገባቸውን ከምርጫ ክልሉ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።
የመራጮች ምዝጋባ በተገቢው መንገድ መጠናቀቁን ያነሱት የምርጫ ክልሉ ሃላፊ አቶ ዮሃንስ ነጋሽ ሰኞ ለሚከናወነው የድምጽ አሰጣጥም የምርጫ ጣቢያዎች ዝግጁ ሆነዋል ብለዋል።
ከዚህ ባለፈ የተወሰኑ የምርጫ ማስፈጸሚያ ቁሳቁሶችን መረከባቸውንና ቀሪዎቹ ነገ ተጠናቀው እንደሚደርሱ አስተባባሪው ተናግረዋል።
የከተማው ነዋሪዎች ለመጪው ምርጫ ድምጽ ለመስጠት መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል፡፡
በቻግኒ የምርጫ ክልል ሰባት የፖለቲካ ፓርቲዎች እንደሚወዳደሩ ታውቋል።
በይስማው አደራው
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.